የኒያላ ሞተርስ 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል
ሀሙስ ግንቦት 10 ቀን 2015
ኒያላ ሞተርስ አክሲዮን ማኅበር 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ሀሙስ ግንቦት 10 ቀን 2015 ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ በተገኙበት ከውድ ደንበኞቹና አጋር ድርጅቶቹ ጋር በመሆን በደማቁ አክብራናል፡፡
እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳንም ደስ አለን!


የሀምሳ አመት የስራ የስኬት የወርቅ እዮብልዩ በዓላችንን ስናከብር በታላቅ ደስታ ነው…በያኔዋ ዘናጭ ዳትሰን አውቶሞቢል ተዋውቀን የታሪክ ትዝታን አኑረናል…ዛሬም ተወዳዳሪ የሌለው ጠንካራ የስራ ልምዳችን ብርታት ሆኖን እንደወትሮው ከፊት እንደሆንን፣ ተሽከርካሪዎችን በአይነትና በጥራት እያስመጣን ወዳጅነታችን ይኸው እንደቀጠለ ነው::
በትጋት ላገለገሉን፣ በስራችን ለደገፉን ለውድ ደንበኞችችንና አጋር ድርጅቶች እንዲሁም ለመላው የኢትዮጰያ ህዝብ ልባዊ የሆነ ምስጋናን እናቀርባለን።እናመሰግናለን።

እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳንም ደስ አለን!
Nyala Motors 50 years anniversary at Sheraton Addis Hotel